የፋይናንስ ድጋፍ እቅድ ለከባድ ወንጀል ተጎጂዎች/ሰለባዎች እርዳታ መስጠት ይችላል። እንደሚከተሉትላሉ ወጪዎችለመክፈል እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ፦
- የምክርአገልግሎት
- የሕክምናወጪዎች
- የገቢማጣት
- ለማገገምየሚረዳዎ ሌላድጋፍ።
የሚከተሉትን ለማድረግ ወደ ፋይናንስ ድጋፍ እቅድ የእርዳታ መስመር መደወል ይችላሉ፦
- ለፋይናንስድጋፍ ለማመልከትእርዳታ ለማግኘት
- ስለ የሚያስፈልግዎት ሰነዶችእና ማስረጃምክር ለማግኘት፣እና
- የማመልከቻውጤቶችን ለመወያየት።
አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ አንድ ሰው ወደ የእርዳታ መስመር ጥሪ እንዲያደርግልዎ እና እንዲጠይቅልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
ወደየእርዳታ መስመርበ 1800 161 136 መደወል ይችላሉ።
የእርዳታመስመሩ ከበዓልቀናት በስተቀር፣ከጥዋት 8፡30-5፡30 ማታድረስ ከሰኞእስከ አርብክፍት ነው።
ብቁነት
በቪክቶሪያውስጥ በከባድወንጀል ምክንያትጉዳት ከደረሰብዎትለእቅዱ ማመልከትይችላሉ። ይህአካላዊ ወይምአእምሯዊ ጉዳትወይም የስሜትቀውስ ሊሆንይችላል።
ወንጀሉን ለፖሊስሪፖርት ማድረግአለብዎት (ለፖሊስሪፖርት ያላደርጉበትልዩ ሁኔታዎችከሌሉ በስተቀር)። ወንጀለኛውሊከሰስ ወይምሊፈረድበት አይገባም።
የተፈጸመውንነገር ከግምትውስጥ በማስገባት፣እንደ አንደኛ፣ ሁለተኛወይም ተዛማጅተጎጂ/ሰለባ ተብለውሊመደቡ ይችላሉ።
አንደኛ ሰለባየሚሆኑት በሚከተሉትሁኔታዎች ነው፦
- ወንጀሉየተፈጸመው በእርስዎላይ ከሆነ
- ወንጀሉንያዩ፣ የሰሙወይም ተጋላጭየሆኑ ህጻንከሆኑ፣ ወይም
- ጉዳትየደረሰብዎት ሌላንተጎጂ ለማዳን፣ከባድ ወንጀሉንለማስቆም ወይምወንጀሉን የፈጸመውንሰው ለመያዝሲሞክሩ ከሆነ።
ሁለተኛ ሰለባየሚሆኑት በሚከተሉትሁኔታዎች ነው፦
- የወንጀሉንድርጊት ከተመለከቱ፣ወይም
- የወንጀሉሰለባ/ተጎጂየሆነ ልጅወላጅ በመሆንዎምክንያት ጉዳትከደርሰብዎ።
ተዛማጅ ሰለባየሚሆኑት በሚከተሉትሁኔታዎች ነው፦
- በከባድወንጀል ምክንያትየሞተ ግለሰብየቅርብ የቤተሰብአባል ከሆኑ
- በከባድወንጀል ምክንያትየሞተብዎት የቅርብሰው ጥገኛከሆኑ፣ ወይም
- በከባድወንጀል ምክንያትየሞተብዎት የሚወዱትሰው ጋርየጠበቀ የግልግንኙነት ውስጥከነበሩ።
በፋይናንስ ድጋፍ የሚሸፈኑ የወንጀሎች ምሳሌ
- ግድያ
- ጥቃት
- አስገድዶመድፈር
- የግድያዛቻ
- ዘረፋ
- በቸልተኝነትምክንያት ጉዳትማድረስ
- ተወቃሽአነዳድ
- ወሲባዊወንጀሎች
- ምስላዊወሲባዊ ወንጀሎች
- መከታተል/ማድባት
- ጠለፋ
- የቤትወረራ
እዚህያልተዘረዘሩ ሌሎችየወንጀል ዓይነቶችለገንዘብ ድጋፍብቁ ሊሆኑይችላሉ።
እቅዱየሚከተሉትን አይሸፍንም፦
- የንብረትጉዳት ወንጀሎች
- የጥቃትእርምጃ ካልተወሰደበስተቀር ጣልቃየመግባት ትዕዛዞችጥሰት።
ሊያገኙ የሚችሉት ነገር
እያንዳንዱሰው ያለበትሁኔታ የተለያየነው። መክፈልየምንችለው መጠንእና የምንከፍልለዎትነገሮች ዓይነትበሚከተሉት ላይይወሰናሉ፦
- ምን ዓይነት ተጎጂ/ሰለባ እንደሆኑ – አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ተዛማጅ ተጎጂ
- በእርስዎ ላይ የተፈጸመው ወንጀል
- በደረሰብዎት ጉዳት።
አንደኛ ሰለባ/ተጎጂ እስከ $60,000 (በአመት በመረጃ ጠቋሚነትላይ በመመሥረትሊጨምር ይችላል) እና ማንኛውምልዩ ክፍያማግኘት ይችላል።
ለደረሰብዎትጉዳት እስከ $25,000 የሚደርስ ልዩ ክፍያየማግኘት ብቁነትሊኖርዎ ይችላል።ይህ ክፍያየሚወሰነው በከባድወንጀሉ እናጉዳትዎ አይነትላይ ነው።
ሁለተኛ እናተዛማጅተጎጂዎች/ሰለባዎችእስከ $50,000 (በአመት በመረጃጠቋሚነት ላይበመመሥረት ሊጨምርይችላል) ድረስሊያገኙ ይችላሉ።
የሚሸፈኑ አገልግሎቶች
ሁሉምተጎጂዎች/ሰለባዎችለሚከተሉት ማመልከትይችላሉ፦
- የምክርአገልግሎትከተመዘገበ የሥነልቦና ባለሙያ፣ከተመዘገበ አማካሪ፣ወይም እውቅናካለው የአእምሮጤና ማህበራዊሠራተኛ
- ምክንያታዊየሕክምና ወጪዎች፣ እና
- ልዩሁኔታ በሚፈጠርበትጊዜ ለማገገምየሚረዱ ሌሎች ወጪዎች።
አንደኛተጎጂዎች/ሰለባዎችለሚከተሉት ማመልከትይችላሉ፦
- የገቢማጣትከጥቃቱ ድርጊትበኋላ እስከ 2 ዓመት ድረስ፣ እስከ $20,000 ድረስ
- በወንጀሉምክንያት (የእጅሰዓቶችን እናጌጣጌጦች ሽፋንአይሰጣቸውም) የተበላሹ ወይምየጠፉ አልባሳት፣ እና
- የአሁኑንደህንነትዎን ለማረጋገጥአስፈላጊ የሆኑእንደ የደህንነትካሜራዎች፣ ሞባይልስልኮች እናየመዘዋወሪያ ወጪዎችየመሳሰሉ የአደጋ መከላከያመሣሪያዎች።
ሁለተኛተጎጂዎች/ሰለባዎችእንዲሁ ለሚከተሉትማመልከት ይችላሉ፦
- የገቢማጣትበልዩ ሁኔታዎች።
ተዛማጅተጎጂዎች/ሰለባዎችእንዲሁ ለሚከተሉትማመልከት ይችላሉ፦
- የሚወዱትሰው ከሞቱበ2 ዓመትውስጥ ከሚወዱትሰው ሊቀበሉይችሉ የነበረውገንዘብ፣ እና
- በሚወዱትሰው ሞትምክንያት የሚኖሩሌሎች ወጪዎች።
ማመልከቻዎንእስክንገመግም ድረስበመጠባበቅ ላይሳሉ፣ የተወሰነውንድጋፍ ወዲያውኑሊከፈልዎት ይችላል።
ይህከጠቅላላው ክፍያዎየሚወጣ ሲሆንእስከ የሚከተሉትሊደርስ ይቻላል፦
- $5,000 ለሕክምና እናለደህንነት ወጪየሚሆን
- $19,627 ለቀብር ወጪዎች
- 5 የምክርአገልግሎት ክፍለጊዜዎች።
የቀብር ወጪዎች
በከባድወንጀል ምክንያትለሞተ ሰውየቀብር ሥነሥርዓት ክፍያየከፈለ ማንኛውምሰው የቀብርሥነ ሥርዓቱንወጪ ለመሸፈንማመልከት ይችላል።
የቀብርወጭዎች ለአንደኛ፣ለሁለተኛ ደረጃወይም ለተዛማጅተጎጂዎች/ሰለባዎችከሚገኘው ከፍተኛመጠን ላይአይቆጠሩም።
ማመልከቻ መሥራት
በማመልከቻዎላይ እገዛከፈለጉ፣ ጠበቃ፣የጉዳይ ሠራተኛወይም ሌላእምነት የሚጣልበትሰው መጠየቅይችላሉ። እንደየእርስዎ የተፈቀደላቸውተወካይ ሆነውመሥራት እንዲችሉቅጽ መሙላትያስፈልግዎታል።
እንዲሁምማመልከቻውን ለማቅረብየጊዜ ገደብአለ።
አዋቂዎችበሚከተለው ግዜውስጥ ማመልከትአለባቸው፦
- ፆታዊወይም የቤተሰብጥቃት ወንጀልበተፈፀመ በ 10 ዓመታት፣ ወይም
- ሌሎችከባድ ወንጀሎችበተከሰቱ 3 ዓመታትውስጥ።
ለልጆችከባድ ወንጀሉየቤተሰብ ጥቃትወይም በልጆችላይ የሚፈጸምጥቃትን የሚያካትትከሆነ የጊዜገደብ የለውም።ለሁሉም ሌሎችወንጀሎች አንድሕፃን 18 ዓመትከሞላው ጀምሮበ3 ዓመትውስጥ ማመልከትአለበት።
በአንዳንድሁኔታዎች፣ እቅዱዘግይተው የሚቀርቡማመልከቻዎችን ሊቀበልይችላል።
እቅዱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ምን ሊከሰት ይችላል?
ማመልከቻዎከተገመገመ በኋላስለ ውሳኔውየጽሑፍ ማስታወቂያይደርስዎታል።
በውሳኔውካልተስማሙ፣ ለውስጥግምገማ ማመልከትይችላሉ። ይህውሳኔ በተሰጠበ28 ቀናትውስጥ መደረግአለበት።
የማመልከቻዎንውጤት ከተቀበሉበኋላ፣ ወደየፋይናንስ ድጋፍዎመቀየር ይፈልጉይሆናል፣ ይህልዩነት ተብሎይጠራል። ይህ ሁኔታዎስለተለወጠ፣ ወይምበሌላ መንገድእርዳታ ስለፈለጉሊሆን ይችላል።
ከእቅዱየገንዘብ ድጋፍየሚያገኙ የወንጀልተጎጂዎች/ሰለባዎችእንዲሁ ለወንጀሉተፅዕኖ እውቅናየሚሰጥ እናየክፍለ-ግዛቱንሀዘን የሚግልጽበቪክቶሪያ ግዛትስም የሆነየእውቅና መግለጫለመቀበል መምረጥይችላሉ።
የወንጀል ተጎጂዎች/ሰለባዎች የእርዳታ መስመር
ይህ ነፃ የእርዳታ መስመር በየቀኑ ከጠዋት 2 ሰዓት–5 ሰዓት ማታ ክፍት ነው። ሲደውሉ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- ስለ ወንጀል ሪፖርት ማድረግ ምክር ማግኘት
- ሊረዱዎት የሚችሉ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት
- ስለ ፍርድ ቤት ሂደት መረጃ ማግኘት።
አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ አንድ ሰው ወደ Victims of Crime (የወንጀል ሰለባዎች) የእርዳታ መስመር ጥሪ እንዲያደርግልዎ እና እንዲጠይቅልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
ወደዚህ ይደውሉ፦ 1800 819 817
Updated